ዜና | Oduu | News
በጉለሌ ክፍለ ከተማ በልዩ ልዩ አገልግሎቶች ለሚሰማሩ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች የመስሪያ ግብዓት ድጋፍ ተደረገ። (ጉለሌ ክ/ከ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት፣ 25 -10 -2018 ዓ.ም )

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ከጂ.አይ .ዜድ (GIZ )ጋር በመተባበር በክፍለ ከተማው በሴፍቲኔት ፕሮግራም ስር ተደራጅተው በቡና ጠጡ እና በእንጀራ መጋገር እና በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ጠንካራ እናቶች፣ ሴቶችና ወጣቶች 100 የዘመናዊ ኤሌክትሪክ ምጣድ፣20 የሻይ ቡና ስቶቭ፣ 30 የምግብ ማብሰያ ምድጃ እንዲሁም 20 የከሰል ምድጃ በአጠቃላይ 170 ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል። በድጋፍ መርሃ ግብሩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ ባስተላለፉት መልእክት እንደገለጹት ልመና እና ተረጂነት አሳፋሪ ተግባር ከመሆኑም በላይ መንግስታችን እንደ አቅጣጫም ይዞ እየተገበረው ያለውና ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር ሰርተው መኖር ለሚችሉ ወገኖች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንደ የጀርመን ተራድዖ ድርጅት እና የመሳሰሉትን በማስተባበር ለእነዚህ በሴፍቲኔት ተጠቃሚ ለነበሩት ወገኖች ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ በጣም ሰብዓዊ እና የሚደገፍ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አቶ ሰለሞን አክለውም ዛሬ ድጋፍ የተደረገላቸው እናቶች ፣ ወገኖችም የተሰጣቸውን የድጋፍ ማቴሪያል በመጠቀም ራሳቸውንም ቤተሰባቸውንም ረድተው ህይወታቸውን በተሻለ ደረጃ ከማድረስ ባሻገር የሚያገኙትን ገንዘብ በመቆጠብ የተሻለ የስራ እድል መፍጠርን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ የእድሉ ተጠቃሚ ወገኖች ራሳቸውን በመቻል ሀገርንም ወገንንም እንዲጠቅሙ ሌሎችም ከእነዚህ በመማር ዜጎች የስራ እድል የሚፈጠርላቸውን ተጠቅመው ራሳቸውን የሚችሉበትን መንገድ አበረታች መሆኑን ሌሎችም ከዚህ ተሞክሮ መማር እንዳለባቸው ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅና የብዝሃ ሕይወት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማናዬ ጫኔ በበኩላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በርካታ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው በዚህ አመት በተለይ በጂ አይ ዜድ ሆፕ ሳይክል በሴፍቲኔት ተጠቃሚ የሆኑትን በማስገባት እራሳቸውን እንዲችሉ የተደረገ መሆኑን እና ሌሎችም ረዳት ድርጅቶች ለእንደነዚህ አይነት ወገኖችን ሰፊ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ይህ ድጋፍ እንዲሁ የተለመደ እርዳታ ሳይሆን እነዚህ ታታሪ የህብረተሰብ ክፍሎች የተደረገላቸውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የምርት ጥራታቸውንና ፍጥነታቸውን እንዲያሳድጉ በዚህም አሁን የጀመሩትን አነስተኛ ስራ ወደ ላቀ ደረጃ በማስፋፋት ለሌሎች ስራ አጥ ወጣቶችና እናቶች አዲስ የስራ ዕድል መፍጠር እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀ ድጋፍ መሆኑም ተገልጿል፡፡ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሃና ምህረቱ በበኩላቸው የኤሌክትሪክ ምጣዶቹና ስቶቮቹ የኃይል ብክነትንና ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ በመሆናቸው ለንግድ ስራው የሚወጣውን ወጪ በመቀነስ ለተጨማሪ ካፒታል ማሳደጊያነት እንዲውል ያደርጋሉ በአንጻሩም የአካባቢ ብክለትን በከፍተኛ ሁኔታ ይከላከላሉ፣ ጭስ አልባና ለአጠቃቀም ምቹ የሆኑት እነዚህ ቴክኖሎጂዎች እናቶችና ወጣቶች ረጅም ሰዓት በስራ ቦታ ሲቆዩ ከጭስና ከተያያዥ የጤና እክሎች ተጠብቀው በሙሉ ጤንነትና ተነሳሽነት ስራቸውን እንዲያከናውኑ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል። በዕለቱ የድጋፉ ተጠቃሚ የሆኑ እናቶችና ወጣቶች በተደረገላቸው ድጋፍ የተሰማቸውን ጥልቅ ደስታና እርካታ በፈገግታና በደስታ ገልፀዋል::

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች መጠቀምን የሚከለክል አዋጅ ተግባራዊ መሆኑ ተገለፀ፡:

በአሁኑ ወቅት የከተሞች መስፋፋት፣ የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የኢኮኖሚ እድገት ሂደትና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች ምክንያት በህዝቡ ዘንድ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚዉሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች ጥቅም ላይ ከዋለ በኋለ በቀጥታ ወደ አካባቢ የሚወገዱ በመሆኑ፤ ይህም የፕላስቲክ ውጤቶች በአፈር ውስጥ ሳይበሰብስ ከአንድ መቶ ዓመት በላይ የሚቆይ በመሆኑ የውሃ አካላት መበከል፤ ብዝሃ ህይወት መጎዳት፣ በምርትና ምርታማነት ላይ ተፅዕኖ ከማድረስ በላይ የሰውንና አካባቢ ጤናን በማወከል ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም ዜጎች በንጽሕ እና ጤናማ አካባቢ የመኖር መብትን ለማረጋገጥ፤ የዜጎችን ጤንነት ከከንሰርና ከሌሎችን በሽታዎች በመከላከል፣ ዘላቂ የአካባቢ አያያዝ ስርዓትን ለማስፈን መንግስት ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ማምረት፣ ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት፣ ማከማቸት፣ መሸጥ እና መጠቀም በደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ 1383/2017 የተከለከለ መሆኑ ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ዜጋ ህጉን በማክበር ራሱን እና አካባቢውን ከፕላስቲክ ብክለት በመከላከል እንዲሁም ከህግ ተጠያቂነት እራሱን በመጠበቅ የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ይህን አዋጅ አፈፃፀም ለማስጠበቅ በክፍለ ከተማው ባሉ አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ከጥር 23 2018ዓ.ም ጀምሮ የቁጥጥር እና ክትትል ስራ መጀመሩን አስታውቋል:: የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደሰሳቹ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ፅ/ቤት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለ2018ዓ.ም የገና በዓል እንኳን አደረሳቹ መልካም በዓል!!

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ አዘጋጅነት በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከ6 ኪሎ ፣ በሽሮ ሜዳ ፣ እንጦጦ የለማው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ጉብኝት ተካሄደ።

በክፍለ ከተማው የለማው የኮሪደር ልማት ስራዎችን በጉብኝቱ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስዩም ከበደ ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ፣ የጉለሌ ክ/ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው : የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን ታደሰ ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንዱ አሰፋ ፣ በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ አመራሮች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ አባገዳዎች ፣ ሀደስንቂዎች ፣ በጎ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ አርቲስቶች፣ ስፖርተኞች እና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ጎብኝተዋል። ለጎብኝዎች ገለጻ ያደረጉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው እንደተናገሩት ባለፉት ዓመታት መንግስት በርካታ ሰው ተኮር የሆኑ ተግባራትን ፣ የማይደፈሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ፣ የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ከቁልቁለት ጉዞ አውጥቶ የማንሰራራት ጊዜያት ላይ ደርሰናል መጪዎች ጊዜያት የከፍታ ዘመን እንዲሆን ሁላችንም በተሰማራንበት ዘርፍ የላቀ ለውጥ የምንተጋበት መሆን ይገባል ብለዋል። የኮሪደር ልማቱ የአስፓልት መንገድ ዝርጋታ ፣የእግረኛ መንገድ ፣ የሳይክል መስመር ፣ የህጻናት መጫወቻ ቦታዎች ፣ የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራዎች ፣ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎችና አረንጓዴ ፓርኮች ፣ መጸዳጃ ቤቶች ፣ የንግድ ሱቆች ፣ የመኪና ማቆሚያና ተርሚናሎች በውስጡ አካቷል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቀነስ ለነዋሪዎቿ ምቹና ጤናማ ክ/ከተማን ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በአየር ንብረት ለውጥ አያያዝ፣ በአካባቢ ብክለት መከላከልና በብዝሃ ሕይወት ዙሪያ በተመለከተ ለተለያዩ ለሲቪክ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በስልጠናው መድረክ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሩ መንግስቱ እንደገለጹት‎ ክፍለ ከተማችን ሰፊ የሆነ የተፈጥሮ ሃብት ክምችት ያላት በመሆኗ ይህንን ሀብት ለመጠበቅና በአግባቡ ለመጠቀም ሰፊ የሆነ አካላዊና ስነ-ሕይወታዊ ስራዎች በመስራት እንዲሁም ከተማችን ከተጋረጠባት ከፍተኛ የብክለት ችግር ለመታደግ የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ብክለት የሚያደርሱ ተቋማት በመለየት ልማት እና አካባቢን ለማጣጣም አካባቢ ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ እንዲሰሩ የማድረግ እንዲሁም ሕብረተሰቡ ስለ አካባቢ ያለዉን ግንዛቤ በተለያየ መንገድ በማሳደግ እና ድጋፍ በማድረግ ለአካባቢ ተቆርቋሪ ሕብረተሰብ ለመፍጠር ጥረት ይደረጋል ብለዋል ፡፡ ‎ ‎በቀጣይም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የአከባቢ ብክለትን በመከላከል የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን እና የአረንጓዴ ልማት ፕሮግራሞችን አጠናክሮ በመስራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስርዓት ለመገንባት በጋራ መረባረብ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡ ‎ ‎

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
አከባቢያችንን ከብክለት ለመከላከል ሁሉም የማህብረሰብ ክፍል የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አከባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በአከባቢ ብክለት፣ በብዝሃ ህይወትና ስነምህዳር እና በአየር ንብረት ለውጥ ዙርያ ለትምህርት ተቋማት የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ አባላት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሀና ምህረቱ እንደተናገሩት በብዝሃ ህይወት ጥበቃ፣ለአከባቢ ብክለትን ተቆርቋሪነት ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ በአከባቢ ላይ የሚደርሱ የአየር ብክለቶችን በመከላከል ንጹህና ጤናማ አካባቢ የመኖር መብትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ የስልጠናው ተሳታፊዎችም የተፈጠረላቸው ግንዛቤ መሰረት በማድረግ አከባቢያቸውን ከብክለት ለመጠበቅና ለመከላከል የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በክረምት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ እንደሚገባ ተገለፀ!!

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የሲቪክ ማህበራት በክረምት መሃግብር የተተከሉ ችግኞችን የውሃ ማጠጣት ፕሮግራም አከናወኑ :: በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ምክትልና ፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ዋቅጋሪ እንደገለፁት ከሆነ በክረምት መርሃግብር በርካታ ንቅናቄዎችን በመፍጠር በርካታ ችግኞች መተከላቸውን የገለፁ ሲሆን ፍሬ እስኪያፈሩ ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካል ተቋማት የሲቪክ ማህበራት ሊንከባከቧቸውና ሊጠብቋቸው እንደሚገባ ገልፀዋል:: የክፍለ ከተማው የብልጽግና የፓለቲካ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሪክተር አቶ ደረጀ ክንፈ እንደገለፁት የሲቭክ ማህበራት ካላቸው ተልህኮ በተጨማሪ በዚህ የችግኝ እንክብካቤ ላይ መሳተፋቸውን አመስግነው እስከመጨረሻው የተክሎቹን እድገት እስክናረጋግጥ እንክብካቤያችንን ማስቀጠል ይኖርብናል በማለት ገልፀዋል::

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የጉለሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ባለሙያዎችና አመራሮች በ2017/18 በክረምት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ውሃ የማጠጣት እና ሌቾች የእንክብካቤ ስራዎችን በዛሬው ዕለት አከናወኑ።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በንግግራቸው እንደሀገር የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ልማት የተስተካከለ የዝናብ ስርጭት እንዲኖር፣ ለኑሮ ተስማሚ የሆነ አካባቢ ለመፍጠር፣ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግና፣ የኢኮኖሚ ጥቅም ለማግኘት ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ችግኝ ተክሎ ማሳደግ የዘውትር ተግባራችን መሆን አለበት ሲሉ ተናግረዋል። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በበኩላቸው በችግኝ እንክብካቤ መርሃ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የመተባበርና የአንድነት ውጤት ማሳያ መሆኑን ገልጸው የሚተከሉ ችግኞች የአየር ንብረት ለውጡን ከመከላከል ባሻገር ለከተማው ውበት የሚሰጡና ለምግብነት የሚውሉ በመሆናቸው መትከል ብቻውን ውጤት ባለመሆኑ የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ የሁላችንም ሃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስርዓትን ለመገንባት የአካባቢ ብክለትን መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አከባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀሙን እና የ2018 በጀት አመት እቅዱን ከሲቪክ ማህበራት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡ ጽ/ቤቱ በተጠናቀቀው በጀት የአየር ፣ የውሃ ፣ የአፈርና የድምጽ ብክለቶች ዙሪያ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመስጠት በወንዝ ዳርቻ ልማቶች ላይ ብክለት መከላከያ መንገዶችን ተግባራዊ በማድረግ ወንዞችን መከላከል መቻሉ የአካባቢ ጥበቃና የልማት ስራዎች ማከናወኑን በሪፖርቱ ላይ ተብራርቷል ። የክፍለ ከተማው አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሃና ምህረቱ እንደተናገሩት በተጠናቀቀው በጀት አመት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና የአካባቢ ግንዛቤ የማጎልበትና ከመቆጣጠር አንፃር ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ በርካታ ስራዎች የተሰሩ መሆኑን በመግለጽ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ልማት የመገንባት ስራውም ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡ እየተተገበረ ላለው የአረንጓዴ ልማት መርሃ-ግብርም የችግኝ በማፍላትና የመትከያ ጉድጓድ በማዘጋጀት፣በመትከልና የጽድቀት መጠን ለማሳደግ በመንከባከብና በመጠበቅ ውጤታማ ስራ ማከናወን መቻሉን ተገልጻል፡፡ በቀጣይም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የአከባቢ ብክለትን በመከላከል የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን እና የአረንጓዴ ልማት ፕሮግራሞችን አጠናክሮ በመስራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስርዓት ለመገንባት በጋራ መረባረብ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡ በተያያዘም የመልካም አስተዳደር ስራዎችና ቅንጅተዊ አሰራሮች ዙሪያ ውይይት አካሄዷል። ጽ/ቤቱ በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላበረከቱ ባለ ድርሻ አካላት ፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ከUNDP ኦርጋናይዜሽንጋር በመተባበር በንብ ማነብ ሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን አባወራዎችና እማወራዎች አሰልጥኖ አስመረቀ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ከUNDP ኦርጋናይዜሽን ጋር በመተባበር ለአየር ንብረት ተጋላጭ ለሆኑ አካባቢዎች በክፍለ ከተማው ወረዳ 6 የእንጦጦ ደን አካባቢ ላይ የሚኖሩ በኑሮአቸው ሊደጎሙ ለሚገቡ የህብረተሰብ ክፍሎች 70 አማወራዎችና አባወራዎች በንብ ማነብ አሰልጥኖ አስመረቀ፡፡ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሃና ምህረቱ እንደተናገሩት እንደ ክፍለ ከተማ ሰው ተኮር የሆኑ ስራዎችን በዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ሲሆን የዛሬው ምርቃት የደን አካባቢ ነዋሪዎች ገቢ መፍጠሪያ እንዲሆን በማድረግ የአካባቢውን ተፈጥሮ ሃብት ተንከባካቢ እንደሆኑ ገልጸው በንብ ማነብ ዘርፍ አሰልጥኖ ስራ ዕድል ዕድል እንዲያገኙ ተሰርቷል ህብረተሰቡ የሚኖርበትን አካባቢ የሚገኘውን የደን ስፍራ ከጎጂ ነገሮች በመጠበቅ የኑሮ ሁኔታዎችን በማሻሻል ጠንክሮ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስልጠና ክፍል ምክትል ኃላፊ አቶ ደመላሽ ተስፋዬ በበኩላቸው ሰልጣኞች በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ያገኙትን ስልጠና ወደ ተግባር መቀየርና ምርትና ምርታማነታቸውን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

image
image
image
image