image
image
image
image
image

በጉለሌ ክፍለ ከተማ በልዩ ልዩ አገልግሎቶች ለሚሰማሩ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች የመስሪያ ግብዓት ድጋፍ ተደረገ። (ጉለሌ ክ/ከ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት፣ 25 -10 -2018 ዓ.ም )

ሰኔ 25, 2018
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ከጂ.አይ .ዜድ (GIZ )ጋር በመተባበር በክፍለ ከተማው በሴፍቲኔት ፕሮግራም ስር ተደራጅተው በቡና ጠጡ እና በእንጀራ መጋገር እና በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ጠንካራ እናቶች፣ ሴቶችና ወጣቶች 100 የዘመናዊ ኤሌክትሪክ ምጣድ፣20 የሻይ ቡና ስቶቭ፣ 30 የምግብ ማብሰያ ምድጃ እንዲሁም 20 የከሰል ምድጃ በአጠቃላይ 170 ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል። በድጋፍ መርሃ ግብሩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ ባስተላለፉት መልእክት እንደገለጹት ልመና እና ተረጂነት አሳፋሪ ተግባር ከመሆኑም በላይ መንግስታችን እንደ አቅጣጫም ይዞ እየተገበረው ያለውና ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር ሰርተው መኖር ለሚችሉ ወገኖች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንደ የጀርመን ተራድዖ ድርጅት እና የመሳሰሉትን በማስተባበር ለእነዚህ በሴፍቲኔት ተጠቃሚ ለነበሩት ወገኖች ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ በጣም ሰብዓዊ እና የሚደገፍ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አቶ ሰለሞን አክለውም ዛሬ ድጋፍ የተደረገላቸው እናቶች ፣ ወገኖችም የተሰጣቸውን የድጋፍ ማቴሪያል በመጠቀም ራሳቸውንም ቤተሰባቸውንም ረድተው ህይወታቸውን በተሻለ ደረጃ ከማድረስ ባሻገር የሚያገኙትን ገንዘብ በመቆጠብ የተሻለ የስራ እድል መፍጠርን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ የእድሉ ተጠቃሚ ወገኖች ራሳቸውን በመቻል ሀገርንም ወገንንም እንዲጠቅሙ ሌሎችም ከእነዚህ በመማር ዜጎች የስራ እድል የሚፈጠርላቸውን ተጠቅመው ራሳቸውን የሚችሉበትን መንገድ አበረታች መሆኑን ሌሎችም ከዚህ ተሞክሮ መማር እንዳለባቸው ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅና የብዝሃ ሕይወት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማናዬ ጫኔ በበኩላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በርካታ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው በዚህ አመት በተለይ በጂ አይ ዜድ ሆፕ ሳይክል በሴፍቲኔት ተጠቃሚ የሆኑትን በማስገባት እራሳቸውን እንዲችሉ የተደረገ መሆኑን እና ሌሎችም ረዳት ድርጅቶች ለእንደነዚህ አይነት ወገኖችን ሰፊ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ይህ ድጋፍ እንዲሁ የተለመደ እርዳታ ሳይሆን እነዚህ ታታሪ የህብረተሰብ ክፍሎች የተደረገላቸውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የምርት ጥራታቸውንና ፍጥነታቸውን እንዲያሳድጉ በዚህም አሁን የጀመሩትን አነስተኛ ስራ ወደ ላቀ ደረጃ በማስፋፋት ለሌሎች ስራ አጥ ወጣቶችና እናቶች አዲስ የስራ ዕድል መፍጠር እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀ ድጋፍ መሆኑም ተገልጿል፡፡ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሃና ምህረቱ በበኩላቸው የኤሌክትሪክ ምጣዶቹና ስቶቮቹ የኃይል ብክነትንና ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ በመሆናቸው ለንግድ ስራው የሚወጣውን ወጪ በመቀነስ ለተጨማሪ ካፒታል ማሳደጊያነት እንዲውል ያደርጋሉ በአንጻሩም የአካባቢ ብክለትን በከፍተኛ ሁኔታ ይከላከላሉ፣ ጭስ አልባና ለአጠቃቀም ምቹ የሆኑት እነዚህ ቴክኖሎጂዎች እናቶችና ወጣቶች ረጅም ሰዓት በስራ ቦታ ሲቆዩ ከጭስና ከተያያዥ የጤና እክሎች ተጠብቀው በሙሉ ጤንነትና ተነሳሽነት ስራቸውን እንዲያከናውኑ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል። በዕለቱ የድጋፉ ተጠቃሚ የሆኑ እናቶችና ወጣቶች በተደረገላቸው ድጋፍ የተሰማቸውን ጥልቅ ደስታና እርካታ በፈገግታና በደስታ ገልፀዋል::

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች