image
image
image
image
image

ቆሻሻን በተገቢው መንገድ በማስወገድ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ እንዲፈጠር እየሰራ መሆኑን የልደታ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ገለጸ።

ጥቅምት 24, 2018
ጽ/ቤቱ ከተማ አቀፍ በማሆበረሰቡ የደረቅ ቆሻሻ ከምንጩ የመለየት ንቅናቄ ማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄደ። በፕሮግራሙ ላይ የጽዳት አምባሳደሮች፣ባለሙያዎች፣የሽርክና ማህበራት፣ ነዋሪዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያየ ዓለም እንደገለጹት የደረቅ ቆሻሻ አያያዝን በማስተካከልና ከምንጩ በመለየት በቅብብሎሽ በማጓጓዝ የሚፈለገው ቦታ በማድረስ አካባቢያችንን በንጽህና በመያዝ ለመኖሪያ ምቹ እንድትሆን በመተባበር ልንሰራ የሚገባ መሆኑን ገልጸዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሓዱሽ ሓጎስ በበኩላቸው የንቅናቄው ዓላማ ቆሻሻን በተገቢው መንገድ የሚበሰብሱ ቆሻሻዎችንና የማይበሰብሱትን ከምንጩ በመለየት ጥቅማ ላይ እንዲውል ለማድረግና ደረቅ ቆሻሻ ከሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ መልሶ ጥቅም ላይ እንዲዉሉ ለማድረግ መሆኑን ተናግረዋል። ደረቅ ቆሻሻን መልሶ ኡደት በማድረግ ይሰጠው ከነበረው አገልግሎት በሙሉ ወይም በከፊል ለሌላ አገልግሎት ማዋል በትኩረት ከተሰራበት የሀብት ምንጭ መሆኑን የገለጹት አቶ ኃዱሽ ደረቅ ቆሻሻን ጥቅም ላይ ለማዋል በሚከናወነው ተግባር የተደራጁ የሽርክና ማህበራት፣ባለሙያዎች፣የጽዳት አምባሳደሮችና ህብረተሰቡ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ደረቅ ቆሻሻን ከምንጩ በመለየት መልሶ የመጠቀም ባህልን ልናሳድግ ይገባል ብለዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት አዲስ አበባ ከተማን ገጽታ የቀየሩ በርካታ የልማት ስራዎች መሠራታቸውን ገልጸው ቆሻሻን በየቦታው ከመጣል ተቆጥበን ቆሻሻን በአግባቡ በመለየትና መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል አካባቢያችን ለመኖሪያ ምቹ የተጀመሩ የልማት ስራዎችም ቀጣይ እንዲሆኑ መስራት የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች